ማሳሰቢያ

ጎብኚዎች ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መገኘት ሲኖርባቸው በተጨማሪም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመሁኔታዎች ካላሟሉ ፓርኩን መጎብኘት አይችሉም።

የሚከለከል

ጎብኚዎች ይዘው መምጣት የሌለባቸው ነገሮች።

  • - ስለት
  • - ተቀጣጣይ ቁሶች
  • - የጦር መሳሪያዎች
  • - ምግብ መጠጦች እና ጣፋጭ ነገሮች
  • - ማስቲካ
  • - የመዋቢያ ቁሶች
  • - የግል ካሜራዎች
  • - ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች
  • - ሲጋራ እና አደንዛዥ ዕጾች
  • - አደንዛዥ ዕፆች
  • - የቤት እንስሳት

ስነምግባር

በፓርኩ ውስጥ ማድረግ የተከለከሉ ተግባራትና ባህሪያት።

  • - በጉብኝት ወቅት ሳርም ሆነ ለዉበት የተቀመጡ ነጫጭ ድንጋዮች መርገጥ፡፡
  • - የተጠቀሙበትን ማንኛዉም ቆሻሻ ባልተፈቀዱ ቦታዎች መጣል፡፡ ለዚህ ጥቅም እንዲዉሉ ተደርገዉ በየቦታዉ የተዘጋጁትን ቅርጫቶች እንዲጠቀሙ እናሳስባለን፡፡
  • - በጉብኝትዎ ወቅት የሚያገኟቸዉን ቅርሶች እንዲሁም የዐዉደ ርዕይ ክፍል ግድግዶች፣ መስታወቶች እና የቪዲዮ ማሳያ ስክሪኖች፣ የመረጃ ማሳያዎች መንካትም ሆነ መደገፍ፡፡
  • - ያለአግባብ ድምፅን ከፍ አድርጎ ማውራትም ሆነ መጮህ እንዲሁም በመሮጥ ሌሎች ጎብኚዎችን መረበሽ፡፡
  • - ህፃናትን ይዘው ወደ ፓርኩ በሚመጡበት ወቅት ህፃናቱን ለብቻቸው መተው፡፡
  • - እንስሳትን ማስፈራራት እና ማስቆጣት፡፡
  • - ቆሻሻ፣ ምግብ እና ሌሎች ነገሮችን በእንስሳቱ መከለያ ውስጥ መጣል፡፡
  • - በፓርኩ ውስጥ ማንኛውም አይነት አደንዛዥ እፅ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡