aquarium1
aquarium1
aquarium1

ወዳጅነት አደባባይ ምዕራፍ አንድ

ወዳጅነት አደባባይ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) አነሳሺነት የተሰራው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት አካል ነው። የወዳጅነት አደባባይ ሰዎች የሚናፈሱበትና የሚዝናኑበት ቦታ ሲሆን፤ ዲዛይኑም የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ አንድነትና የባህል ብዝኃነት ያንፀባርቃል፡፡ አደባባዩ በቻይና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት አምሳኛ ዓመት ለማክበር በቻይና ምንግስት ድጋፍ የተገናባ ነው፡፡ ይህ ፓርክ 32 ሄክታር ስፋት ያለው ሲሆን ከ6000 በላይ እፅዋት በዘመናዊ የንቅለ ተከላ መንገድ በሌሎች ቦታዎች የበቀሉ ዛፎች ተጓጉዘው መጥተው የተተከለበት የአረንጓዴ ልማት ተምሳሌት የሆነ ስፍራ ነው። ይህ ፓርክ በውስጡ የሥነ-ሥርዓታዊ ዝግጅት አደባባይ፣ የጥበብ አትክልት ስፍራን፣ ባህላዊ ጉብጉብ ግድግዳ፣ ሰው ሰራሽ ሐይቅ፣ የውሃ እና መብራት ዳንስ ማሳያ ቴክኖሎጂ፣ መካነ ዘንባባ፣ የአበባ ጅረት፣ የአትክልት ሥፍራ የጥበብ ማዕከልን፣ ካፍቴሪያዎች እና ሌሎች መዝናኛዎችን ያካተተ ነው። ፓርኩ ከመዝናኛነት አልፎ ለሙሽሮች እና ለሌሎች ፕሮግራሞች ተመራጭ የፎቶ መነሻ ቦታ ሆኖ እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን፤ በተጨማሪም ትልልቅ ሃገራዊ እና ግለሰባዊ ፋይዳ ያላቸውን መርሃ-ግብሮች በማካሄድ ሁነኛ የጉብኝት መዳረሻ እና የመርሃ ግብር ማካሄጃ አማራጭ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም ጎብኚዎች ለጠዋት እና ምሽት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚመርጡት ስፍራ ለመሆን በቅቷል።

አድራሻ፡ ሸራተን አዲስ ሆቴል ፊትለፊት
ስልክ ቁጥር፡ +251118550140
የፌስቡክ ገፃችን፡ Friendship Square - የወዳጅነት አደባባይ