የፓርኩ የአገልግሎት ቀንና ሰዓት

አንድነት ፓርክ ዘወትር ከሰኞ በስተቀር ከማክሰኞ እስከ እሁድ በዓላትን ጨምሮ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ብቻ ለጎብኚዎች የመግቢያ ትኬት የሚያቀርብ ሲሆን ፤የፓርኩ የጉብኝት ማብቂያ ሰዓት ደግሞ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ነው፡፡
ማስታወሻ፡- የአንድነት መኪና ማቆሚያ ግን 24 ሰዓታት አገልግሎት ይሰጣል!

የትኬት ዓይነቶች

በዚህ የትኬት ዓይነት ጎብኚዎች ከአጼ ምኒልክ ቤተ መንግስት እልፍኞች (ዕንቁላል ቤት) ውጪ ያሉ ዘጠኙን መዳረሻዎች ያለአስጎብኚ በራሳቸው መጎብኘት የሚችሉበት የትኬት ዓይነት ነው፡፡

ይህ የትኬት ዓይነት ለጎብኚዎች በዋናነት 3 ዓይነት ጥቅሞች ይሰጣል፡፡ ጎብኚዎች በትኬት መቁረጫና ፍተሻ አጭርም ሆነ ረጅም ወረፋ ቢኖር ቅድሚያ ያገኛሉ፤ በተለያዩ ቋንቋዎች አስጎብኚ ይመደብላቸዋል እንዲሁም በመደበኛ ትኬት ከሚታዩት ስፍራዎች በተጨማሪ ከፓርኩ ታሪካዊ ህንፃዎች ውስጥ የአጼ ምኒልክ ቤተ-መንግስት እልፍኞች (ዕንቁላል ቤት) እና በውስጡ የያዘውን ልዩ ልዩ ቅርሶችን መጎብኘት የሚችሉበት የትኬት ዓይነት ነው፡፡ (ማስታወሻ፡-ይህን ትኬት የሚገዙ ጎብኚዎቻችን የተሟላ ጉብኝት እንዲኖራቸው በማሰብ ፓርኩ ከቀኑ 9 ሰዓት በኋላ የልዩ ትኬት አይሸጥም፡፡)

በዚህ ትኬት የሰርግ፤ የልደት፤ የምርቃት እና የእናትነት የመስክ ፎቶና ቪዲዮ አገልግሎት ፈላጊዎች ብቻ የሚስተናገዱበት ትኬት ነው፡፡ (በልዩ ሁኔታ እስካልተፈቀ ድረስ በፓርኩ ውስጥ የቴሌቪዥን ፕሮግራም፣ ማስታወቂያ፣የፊልም ቀረፃ፣ የፋሽን ትርዒት እና የመሳሰሉትን ማከናወን ወይም ለዚህ ዓይነት መርሐግብሮች የፓርኩን ምስሎች መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡)

የትኬት ዓይነቶችና የሚሰጡ ልዩ ልዩ የአገልግሎት ጥቅሎች

የጥቅል ዓይነቶች ለኢትዮጵያውያን ለውጭ አገር
የመደበኛ ጉብኝት ጥቅል 300 ብር 20 የአሜሪካ ዶላር
የልዩ ትኬት ጉብኝት ጥቅል 1100 ብር 50 የአሜሪካ ዶላር
የፎቶግራፍ ጥቅል (ለሰርግ፤ለልደት፤ለምርቃና ለእናትነት) ብቻ 1000 ብር በሰው 50 የአሜሪካ ዶላር በሰው
በት/ቤት ለሚመጡ ተማሪዎች የሚሰጥ ጥቅል 150 ብር በሰው 10 የአሜሪካ ዶላር በሰው
ማስታወሻ* የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያላቸው ጎብኚዎች የመግቢያ ክፍያ እንደ ኢትዮጵያዊ የሚከፍሉ ሲሆን፤ ይህንን ጥቅም ለማግኘት የታደሰ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡

ማስታወሻ፡-

- ለመደበኛና ለልዩ የትኬት አገልግሎት ፈላጊዎች ሁሉም ክፍያዎች ዕድሜያቸው ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆናቸው ማንኛውም ጎብኚዎች ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ለፎቶግራፍ አገልግሎት ፈላጊዎች በፎቶግራፍ ጥቅሉ ውስጥ ተካተው የሚገቡ በሁሉም ዕድሜ ላይ ያሉ ሰዎችን የተጠቀሰው የመግቢያ ዋጋው ያካትታል፡፡
- በትምህርት ቤት በቡድን ለሚመጡ ተማሪዎች ፓርኩ የሚሰጠውን የመግቢያ ዋጋ ቅናሽ ተጠቃሚ ለመሆን ት/ቤቶቹ ከጉብኝት ቀናቸው 3 ቀናት በፊት ለፓርኩ የተጻፈ የትብብር ደብዳቤ ይዘው መቅረብና አስፈላጊ መረጃዎችን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ:- ለምግብና መጠጥ ወይም ለግብይት ፍላጎትዎ የተለያዩ ካፌና ሬስቶራንቶች እንዲሁም የጌጣጌጥና የስጦታ ዕቃዎች መሸጫ ተቋማት በፓርኩ ውስጥ ያሉ ሲሆን ለጥሬ ገንዘብ ፍላጎትዎም የATM ማሽኖች አሉ፡፡

የፓርክ መግቢያ የክፍያ አማራጮች

1. በፓርኩ መግቢያ ላይ ከሚገኘው የትኬት ቢሮ ለጉብኝት በሚመጡበት ወቅት በጥሬ ገንዘብ (በብር ወይም በውጭ ሀገር መገበያያ ገንዘቦች) ከፍሎ መግባት ይቻላል፡፡

2. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም በፓርኩ የሂሳብ ቁጥር 1000294128388 ወይም አጭር ቁጥር 6030ን በመጠቀም ከፍሎ መግባት፡፡

3. ማንኛውንም የሀገር ውስጥ ባንክ ወይም ዓለም-አቀፍ ካርዶችን በመጠቀም በፖስ ማሽን ክፍያን በመፈጸም ይቻላል፡፡

4. በቴሌብር ሱፐር-አፕ ወይም *127# ትኬት ለመግዛት በሚለው አማራጭ የአንድነት ፓርክን በመምረጥ የመግቢያ ክፍያን ከፍሎ መግባት፡፡ በቴለብር ሱፐርአፕ ‘ተጨማሪ’ የሚለውን መምረጥ ቀጥሎ ‘ትኬት ለመግዛት የሚለውን መምረጥ ቀጥሎ ‘አንድነት ፓርክ’ የሚለውን መርጦ ትኬት መግዛት ይቻላል። *127# ለመግዛት መጀመሪያ ከተዘረዘሩት አማራጮች ‘በቴሌብር ይክፈሉ’ ወይም 8 ቁጥር መምረጥ ቀጥሎ ‘ትኬት ለመግዛት’ ወይም 4 ቁጥር የሚለውን መምረጥ ቀጥሎ ‘አንድነት ፓርክ’ የሚለውን መርጦ ትኬት መግዛት ይቻላል።