aquarium1
aquarium1
aquarium1

ሳይንስ ሙዚየም

የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት ምዕራፍ 2 አካል ሲሆን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል ነው፡፡ ሙዚየሙ በ7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን እንደ ሌሎቹ የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክቶች በአርንጓዴ መስኮች እና የአበባ ሰገነቶች ያጌጠ ሃገራችንን የተያያዘችው የአረንጓዴ ልማት ማሳያ አንዱ ምልክት ነው። ይህ ሙዚየሙ ከሃገር ገፅታ ግንባታ አልፎ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ምሁራንና ፣ የነገውን ሃገር ተረካቢ ትውልድ ለበለጠ ጥናት እና ምርምር የሚያነሳሳ ማዕከል ነው፡፡ ሙዚየሙ የቋሚና ጊዜያዊ አውደ ርዕይ ክፍሎችን፣ የዲዛይን ላቦራቶሪ፣ የጥናትና ምርምር ክፍሎች፣ የልዩ እንግዶች ማስተናገጃ ክፍሎች፣ የመቆጣጠሪያ ክፍሎች፣ ለካፌና ሌሎች ግልጋሎቶች የሚውሉ ክፍሎችን በውስጡ አቅፎ ይገኛል። በሙዚየሙ በሃገራችን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ፕላኒቴሪየም የሚገኝ ሲሆን ስነህዋን እና የጠፈር አካላትን በቀላል መንገድ ለመረዳት የሚያስችል ነው። ይህ 24 ሜትር የሚረዝም የፕላኒቴሪየም ህንፃ 200 ተመልካቾችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግድ፣ ስሪዲ ቪዲዮዎች እና ዘጋቢ ፊልሞች የሚታዩበት ነው። ይህ ሙዚየም ተመርቆ ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ጊዜያዊ አውደ ርዕዮችን ያስተናገደ እና ሚሊዮኖች የጎበኙት ስፍራ ነው።

አድራሻ፡ አንድነት ፓርክ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡ +251933598330
የፌስቡክ ገፃችን፡ የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም Science Museum