aquarium1
aquarium1
aquarium1

ወዳጅነት አደባባይ ምዕራፍ 2

ይህ ፓርክ የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት ምዕራፍ 2 አካል ሲሆን በከተማችን የሚስተዋለውን የአረንጓዴ ስፍራዎች እጥረት የቀረፈ እና የተፋሰስ ልማት ስራን እውን ያደረገ ነው። የፓርኩ አጠቃላይ ስፋት 11 ሄክታር ሲሆን፤ ፓርኩ ውብና ማራኪ እንዲሆን ያስቻሉት ከ4000 በላይ እጽዋት በእጽዋት ንቅለ ተከላ ዘዴ ተጓጉዘው የተተከሉ ናቸው። ይህ ፓርክ የህፃናት መጫወቻ ስፍራዎችን፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎችን እና መሳሪያዎች፣ የሰርግ አፀድ እና ሌሎች መዝናኛዎችን በውስጡ አቅፎ የሚገኝ ነው። የህፃናት መጫወቻ ስፍራው በውስጡ እጅግ ዘመናዊ በሆኑ እና ደረጃቸውን በጠበቁ የመጫወቻ መሳሪያዎች የተደራጀ፣ የህፃናት መዝናኛና ማረፊያ ህንፃ ያለው፤ በቂና የተሟላ የመታጠቢያና ንፅህና መጠበቂያ ክፍሎችን አካቶ የያዘ ነው። ከስፖርት ማዘውተሪያ አንፃር ፓርኩ መለስተኛ የእግር ኳስ ሜዳ፣ የቅርጫት ኳስ መጫወቻ ሜዳዎች እና በመሳሪያ ለሚሰሩ ስፖርቶች የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎች ይገኛሉ። በፓርኩ የሚገኘው የሰርግ አፀድ ዘመናዊ ፋውንቴኖች፣ የሰርግ መድረክ ፣ እንዲሁም ዘመናዊ የድምፅ ማጉያ መሳሪያዎች ተሟልቶለት የተገነባ ሲሆን የሰርግ እና ሌሎች ኩነቶች የሚስተናገዱበት ነው። ፓርኩ በርካታ ተሸከርካሪዎችን ለማስቆም የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ እንዲሁም ህፃናትና ቤተሰቦቻቸው የሚዝናኑባቸው ካፌዎችና ሬስቶራንቶችን አቅፎ የያዘ ስፍራ ነው፡፡ በተጨማሪም ፓርኩ የጋብቻ የመስክ ፎቶ፣ የልደት ፎቶ እና ሌሎች የፎቶግራፍ አገልግሎቶች የሚስተናገዱበት ውብ ስፍራ ነው።

አድራሻ፡ አብርሆት ቤተ መፃህፍት ጎን
ስልክ ቁጥር፡ +251933598330
የፌስቡክ ገፃችን፡ Friendship Square Phase 2- የወዳጅነት አደባባይ ምዕራፍ 2