-    ማንኛውም ጎብኚ ወቅታዊ ዜግነቱን/ማንነቱን ማሳየት የሚችል የታደሰ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፤ መንጃ ፈቃድ፤ ፓስፖርት ወዘተ...) አንዱን ይዞ መገኘት አለበት፡፡
-    የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያላቸው ጎብኚዎች የመግቢያ ክፍያ እንደ ኢትዮጵያዊ የሚከፍሉ ሲሆን፤ ይህንን ጥቅም ለማግኘት የታደሰ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
-    በኢትዮጵያ የመኖሪያ ፈቃድ መታወቂያ ይዘው የሚመጡ የውጭ ሀገር ዜጎች የመግቢያ ክፍያን የሚከፍሉት እንደ ውጭ ሀገር ዜጋ ነው፡፡
- ማንኛውም ዓይነት የጦር መሳሪያዎችና የጦር መሳሪያ አካላት፤
- ስለታማ ነገሮች፤
- ማንኛውም ዓይነት ኬሚካልና ንጥረ ነገሮች፤
- ከህጻናት ምግብ በስተቀር ማንኛውም ዓይነት ምግብና መጠጥ፤
- ፓወር ባንክ፤ ዋይፋይ ራውተር፤ ፍላሽ ዲስክና ሀርድ ዲስክ፤
- መድሃኒቶች፤
- ማንኛውም አደንዛዥ እጽ (እጽ፣ ሲጋራ፣ ኤሌክትሮኒክ ሲጋራ፣ ጫት፣ አልኮል እና የመሳሰሉት)
- ቴፕ መቅጃ፤
- የግል ካሜራዎችና የካሜራ ድሮን፤
- ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች (ላፕቶፕ፣ ኪቦርድ፣ ስፒከሮች እና የመሳሰሉት)
- ማንኛውም ፈሳሽ ነገሮች (ጄል፣ ስሞቲክስ እና የመሳሰሉት)
- ለአገልግሎቱ ክፍያ ካልፈጸሙ በቀር የሙሽራ፣ የልደት፣ የምርቃት እና ሌሎች ኩነቶች አልባሳት
- የቤት እንስሳት ወዘተ …
- በጉብኝት ወቅት ሳርም ሆነ ለዉበት የተቀመጡ ነጫጭ ድንጋዮች መርገጥ የተከለከለ ነው።
- አበባ፣ ቅጠል እና የዛፍ ቅርንጫፍ መቁረጥ የተከለከለ ነው፡፡
- የተጠቀሙበትን ማንኛዉም ቆሻሻ ለዚህ ጥቅም እንዲዉሉ ተደርገዉ በየቦታዉ በተዘጋጁ ቅርጫቶች እንዲጥሉ እናሳስባለን፡፡
- በጉብኝትዎ ወቅት የሚያገኟቸዉን ቅርሶች፣ የዐዉደ ርዕይ ክፍል ግድግዳዎች፣ መስታወቶች፣ ቪዲዮ ማሳያ ስክሪኖች እና ሌሎች የመረጃ መስጫዎችን መንካትም ሆነ መደገፍ የተከለከለ ነው፡፡
- ያለአግባብ ድምፅን ከፍ አድርጎ ማውራትም ሆነ መጮህ እንዲሁም በመሮጥ ሌሎች ጎብኚዎችን መረበሽ የተከለከለ ነው፡፡
- የግል ፎቶና ቪዲዮ በመነሳት/በመቀረጽ ምክንያት ጎብኚዎችንና የጉብኝት ስርዓትን መረበሽና ማደናቀፍ የተከለከለ ነው፡፡
- ህፃናትን ይዘው ወደ ፓርኩ በሚመጡበት ወቅት ህፃናቱን ለብቻቸው መተው የተከለከለ ነው፡፡
- እንስሳትን ማስፈራራት እና ማስቆጣት እንዲሁም ቆሻሻ፣ ምግብ እና ሌሎች ነገሮችን በእንስሳቱ መከለያ ውስጥ መጣል የተከለከለ ነው፡፡
- በፓርኩ ውስጥ ማንኛውም አይነት አደንዛዥ እፅ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
- ጉብኝት ፈጽመው ከፓርኩ እስኪወጡ ድረስ የጎብኚ መለያ የእጅ ምልክትን ከእጅ መበጠስና መጣል የተከለከለ ነው፡፡
- በፓርኩ ህግና ደንብ መሰረት ከከፈሉት የጉብኝት/የፎቶግራፍ ጥቅል ውጪ ሌላ አገልግሎት በሚሰጥበት ትኬት መገኘት የተከለከለ ነው፡፡